ማህበራዊ ተሳትፎዎች ላይ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ የጊፍት ሪልስቴት ባለቤትና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ ጥሪ አቀረቡ።

  • 2 months ago
  • NEWS
  • 2

Leave a Comment / News / By GIFT Real Estate

ጊፍት ሪል እስቴት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ጋር በመተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ያስገነባውን የመኖሪያ ህንፃ አስርክቧል፡፡

ቤቶቹ ለ30 አቅመ ደካሞች፣ የሀገር ባለውለታዎች እና አካል ጉዳተኞች እንዲውል ተደርጓል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የተገነባው ይህ ዘመናዊ ባለ 4 ወለል የጋራ መኖሪያ ህንፃ 10 የስቱዲዮ፣ 5 ባለ 2 መኝታ እና 15 ባለ አንድ መኝታ ቤቶችን አካትቷል።

የመኖሪያ ቤት ቁልፎቹን ለነዋሪዎች ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ከተማ አስተዳደሩ ከግል አልሚዎች ጋር በመተባበር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከለውጡ ወዲህ 35 ሺህ ያህል ቤቶችን ለነዋሪዎች ማስረከቡን የጠቀሱት ከንቲባዋ፤ ከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

ህንፃውን ያስገነባው ጊፍት ሪል እስቴት ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ ባደረገላቸው ጥሪ በ3 ወራት ውስጥ ህንፃውን አጠናቆ ማስረከቡን ተናግረዋል።

ሪል እስቴቱ ከዚህ ቀደምም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ባለ5 ወለል የመኖሪያ ህንፃ ገንብቶ ማስረከቡን አስታውሰው፤ የማህበራዊ ተሳትፎዎች ላይ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በቁልፍ ርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ለግንባታው አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

Join The Discussion

2 thoughts on “ማህበራዊ ተሳትፎዎች ላይ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ የጊፍት ሪልስቴት ባለቤትና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ ጥሪ አቀረቡ።”

  • Travis

    Hi! This is my first visit to your blog! We are a group of volunteers and starting a new initiative in a community in the same niche.
    Your blog provided us valuable information to work on. You have done a wonderful job!

    my web blog: Construction Company Fife

    Reply
    • admin

      thanks more

      Reply

Compare listings

Compare