የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ የቦርድ አባላት፣ የማኔጅመንት አባላት፣ መላ ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረላቸው እንግዶች በተገኙበት ዓመታዊ የሰራተኞች ቀንን በድምቀት አክብረዋል፡፡
በበዓሉ ወቅት የቢዝነስ ግሩፑ እህት ኩባንያዎች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በዕለቱ በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሰራተኞች የእውቅናና ምስጋና ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በ2016 በጀት ዓመት የነበሩ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመትም የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ርብርብ እንዲደረግ ዋና ስራ አስፈጻሚው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Join The Discussion