ጊፍት ሪል ስቴት የድርጅቱን የብራንድ አምባሳደር ለህዝብ በይፋ አስተዋወቀ


ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በሪል ስቴት ኢንዱስትሪ በዘላቂነት የቆየው ጊፍት ሪል ስቴት የብራንድ አምባሳደሩን ይፋ አድርጓል፡፡

የጊፍት አምባሳደር ጊፍት ሪል ስቴት በሽያጭ እና በማርኬቲንግ ሙያተኞቹ የሚያከናውናቸው መጠነ ሰፊ ሽያጭና ደንበኞችን የማፍራት ተግባራትን በተሳለጠ አግባብ ያግዛል፡፡

ጊፍት ታዋቂውን የኪነጥበብ እና የሚዲያ ሰው አብርሃም ወልዴን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የድርጅቱ አምባሳደር አድርጎ ውል ተፈራርሞ በመሰየሙ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ በጊፍት ደንበኞች፣ ቤተሰቦችና አጋሮች ስም ይገልፃል፡፡

የጊፍት ሪል ስቴት አምባሳደርም ይህንን አዲስ የጊፍት አቅጣጫ በዛሬው ዕለት ውል በመፈራረም ማስተዋወቅ የሚጀምርበት እለት ነው፡፡

የጊፍት አምባሳደር አብርሃም ወልዴም ጊፍት “ማህበረሰብን እንገነባን!” በሚል መሪ ቃል በሪል ስቴት ኢንዱስትሪው ውስጥ በፅናት ከፍተኛ ሚና በመጫውት ላይ ለሚገኘው ድርጅታችን ለሚያደርገው ያላሰለሰ አምባሳደራዊ አበርክቶ መልካሙን ከአደራ ጭምር ይመኛል፡፡

የብራንድ አምባሳደራችን በስነጥበቡ እና በሚዲያው አለም በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ዝናን እየተጎናፀፈ በመምጣት በዘርፉ ታዳጊ ተተኪዎችን በማስተማር፣ በመኮትኮት እና በማፍራት ይታወቃል፡፡

ድርጅታች ታዋቂው የፊልም እና የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር፣ በአገራችን ባህል እና ወግ የተቃኘ፣ አልፎ ተርፎም የአገራችንን ኪነጥበባዊ እሴቶች ከአለም አቀፉ የዘርፉ ሙያ ጋር እንዲጣጣም የራሱን አሻራ በማሳረፍ ላይ የሚገኝ አመለ ሸጋ እና መልካም ዜጋ ነው፡፡

Join The Discussion

Compare listings

Compare