ጊፍት ሪል እስቴት በአጭር ኮድ የስልክ ጥሪ መቀበያ ስርዓት ይፋ አደረገ

  • 4 months ago
  • NEWS
  • 0

ጊፍት ሪል እስቴት አሰራሩን ይበልጥ በማዘመን መረጃዎችን ለደንበኞቹ ተደራሽ የሚያደርግበት በአጭር ኮድ የድምፅ ስልክ ጥሪ መቀበያ ስርዓት ይፋ አድርጓል፡፡

ይህን የድምፅ ስልክ ጥሪ መቀበያ 8055 በይፋ ስራ ላይ መዋል የጀመረ ሲሆን በነጻ ስልክ ጥሪው መረጃዎችን ቀልጣፋና ወጥ በሆነ መልኩ ለደንበኞቹ ተደራሽ ማድረግ ያስችላል፡፡

በዚህ የስልክ ጥሪ መሰረት ጊፍት ሪል እስቴትን የሚመለከቱ፣ በሽያጭ ላይ ስለሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች እና ንግድ ሱቶች እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ስርዓቱ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በ 8055 ነጻ የስልክ ጥሪ ማግኘት ይችላሉ።

Join The Discussion

Compare listings

Compare