ጊፍት ሪል ስቴት የድርጅቱን ብራንድ ይፋ አደረገ


ጊፍት ሪል ስቴት አዲስ የድርጅቱን ብራንድ ይፋ አድርጓል፡፡

አዲሱ የጊፍት ብራንድ ድርጅቱን ከዘመኑ ጋር እያዘመነ፣ በተሻለ እና በተስማሚ ቴክኖሎጂ፣ “ማህበረሰብን እገነባለን!” በሚል መርሁ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን መገንባት መጀመሩን ለህዝብ የሚያበስርበት ነው፡፡

ብራንዱ የጊፍት ሪል ስቴት ደንበኞች፣ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን ሲገዙ እና ምርቱን ሲገለገሉ፣ ከምርቱ ጥራት፣ ከዋጋው ተመጣጣኝነትና በተለይም የጊፍት ሪል ስቴት ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች እና መርህ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በመፍጠር፣ የምርት ትውውቅ ማድረግ ያስችላል፡፡

እንዲሁም በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የሚገኙ የጊፍት ደንበኞችን፣ አጋሮችን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትን ማፍራት እና አዎንታዊ ስሜቶችን እንዲለማመዱ ያስችላል፡፡

ጊፍት እስከ አሁን ባደረገው ጉዞ፣ ከ150 ሺህ ካሬ በላይ በሆነ ቦታ ላይ ሶስት ዘመናዊ መንደሮችን በሲኤም ሲ እና ፈረስ ቤት አካካቢ ገንብቶ አስረክቧል፡፡

የልማት ግስጋሴውን በመቀጠል፣ አሁንም በአዲስ አበባ እምብርት በቦሌ፣ በአትላስ፣ በለገሃር፣ በ22፣ በስድስት ኪሎ፣ በተክለኃይማኖትና በፊጋ አካባቢዎች ዘመኑን የዋጁ ወለላቸው ከ20 በላይ የሆኑ ዘመናዊ መንደሮችን፣ የንግድ እና የመኖሪያ አፓርትማዎች እና ሞሎችን ግንባታ እና ዲዛይን ጀምሯል፡፡

አብዛኞቹ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ ናቸው፡፡

Join The Discussion

Compare listings

Compare