ጊፍት ሪል ስቴት በመንግሥትና የግል አጋርነት ማዕቀፍ 4 ሺህ ቤቶች በላቀ ጥራት ለመገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

  • 4 months ago
  • NEWS
  • 0

ጊፍት ሪል ስቴት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት በመንግስት እና የግል አጋርነት ልማት ፕሮግራም በለገሀር የመኖሪያ መንደር ልማት ፕሮጀክት 4 ሺህ ቤቶች ለመገንባት ስምምነት አካሂዷል፡፡

ሪል ስቴቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የግንባታ ማስጀመሪያ ስምምነት አካሂዷል፡፡

ስምምነቱ በጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ተከናውኗል፡፡

በዚሁም መሰረት በመጀመሪያው ዙር 3 ሺህ 540 የመኖሪያ ቤቶችን፣ 460 ለሱቅ፣ ለትምህርት ቤትና ለሌሎቸ አገልግሎቶች የሚውሉ ሁለገብ ቤቶችን በመሃል አዲስ አበባ ለገሃር አካባቢ የሚገነቡ ይሆናል፡፡

ግንባታው በሶስት ዓመታት የሚጠናቀቅ ነው የሚሆነው፡፡

የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ ጊፍት ሪል ስቴት በመንግሥትና የግል አጋርነት ማዕቀፍ 4 ሺህ ቤቶች በላቀ ጥራት ለመገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን በስምምነቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በሚደረጉ ስምምነቶች ጊፍት ሪል ስቴት ተጨማሪ 8 ሺህ የሚደርሱ ቤቶችን ለማልማት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም አቶ ገ/የሱስ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት በበኩላቸው ፕሮጀክቱ የከተማዋን የቤት አቅርቦት ችግር ከማቃለል ባሻገር ለመዲናዋ ውበት የሚያጎናጽፉ ዘመናዊ ቤቶች እንደሚሆኑ ገልጸዋል ።

Join The Discussion

Compare listings

Compare