በጊፍት ሪልስቴት ስፖንሰርነት የተካሄደው የባላገሩ ምርጥ የፍጻሜ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡

  • 5 months ago
  • NEWS
  • 0

በጊፍት ሪልስቴት ስፖንሰርነት ላለፋት ሦስት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው የባላገሩ ምርጥ በሚሊኒየም አዳራሽ ፍፃሜውን አግኝቷል።

በሚሊኒየም አዳራሽ በተደረገዉ የባላገሩ ምርጥ የፍጻሜ ዉድድር ድምጻዊ አክሊሉ አስፋው የሶስት ሚሊዮን ብር ሽልማትን አሸንፏል።

ለድምፃዊ አክሊሉ አስፋው አንድ ሚሊዮን ብር በግል የሚሰጠው ሲሆን ቀሪው ሁለት ሚሊዮን ብር ለአልበም ስራ ይውላል።

ሽልማቱን ከጊፍት ሪልስቴት ባለቤትና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ እጅ ተቀብሏል፡፡

በውድድሩ ድምጻዊ ብሩክ ሙሉጌታ ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ ድምጻዊ ቅዱስ ዳምጤ እና ድምጻዊ እስማኤል መሀመድ በጋራ የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አሸናዊ ሁነዋል፡፡

ጊፍት ሪልስቴት ላለፉት ሶስት ዓመታት አብረው ለሰሩት የባለገሩ ቤተሰቦች፣ ዳኞች እና ድምጻዊያን ለልብ የመነጨ ምስጋና ያቀርባል፡፡


Join The Discussion

Compare listings

Compare