በሽያጭ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

  • 4 months ago
  • NEWS
  • 0

ጊፍት ሪልስቴት በሽያጭ ዘርፍ ለተሰማሩ 140 አዲስ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው አዳዲስ ክህሎቶችን በመቅሰም የሽያጭ መጠንን ለመጨመር፣ ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ እና ከሌሎች አቻ ድርጅቶች ጋር ጤናማ ውድድርን በመፍጠር ሽያጭን እንዲያሸንፉ የሚያግዙ የማስፈጸሚያ ስልቶችን እንዲያዳብሩ ያግዛል።

የዘርፉ ባለሙያዎች የአሸናፊነት ስነልቦናን በመላበስ፣ ግንኙነትን በማሻሻልና የድርጅቱን መልካም ስም በማጎልበት ስራዎቻቸውን በአግባቡ መከወን እንዲችሉ ያለባቸውን ማነቆ እንዲፈቱ የሚያግዝ ነው።

ለአንድ ቀን በተሰጠው ስልጠና ለሽያጭ የሚያበረታቱ የማነቃቂያ ስልጠናዎች፣ በዲጂታል መንገድ እንዴት ግብይት መፈጸም እንደሚቻል እንዲሁም ስለጊፍት አጠቃላይ አመሰራረት፣ ተገንብተው ስለተጠናቀቁና በግንባታ ላይ ሆነው በሽያጭ ላይ ስለሚገኙ መንደሮች የሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተካተውበታል።

በስልጠናው የነባር የሽያጭ ሱፐርቫይዘሮች፣ ማናጀሮችና ዳይሬክተሮች ልምድና ተሞክሮቻቸውን አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም በዓመቱ በጊፍት ሪል ስቴት የሽያጭ ሙያ ተሰማርተው የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ማናጀሮችና ባለሙያዎች ከድርጀቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እጅ እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል

Join The Discussion

Compare listings

Compare