መቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ሰራተኞች ምስጋና አቀረቡ

  • 10 months ago
  • NEWS
  • 0

መቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለተደረገላቸው ድጋፍ ለጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለመላ የግሩፑ ባለቤት፣ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤናና የስኬት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ በማዕከሉ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን በማድነቅ በቀጣይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትን ማሳደግ የሚያስችሉ ሁለንተናዊ ድጋፎች እንደሚደረጉ ተናግረዋል፡፡

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጅመንትና ሠራተኞች የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ 3 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የምግብ፣ አልባሳትና የዕርድ ከብት ማበርከታቸው ይታወሳል።

Join The Discussion

Compare listings

Compare