ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።


የትንሳኤ በዓል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ከባርነት ቀንበር ወደ ነጻነት የተላለፉበት፤ ከከባድ ሀዘን ወደ ፍጹም ደስታ የተሸጋገሩበት የክርስቶስን ትንሣኤ የምናከብርበት ዕለት ነው፡፡

ይህ በዓል ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፤ ከውርደት ወደ ክብር፤ ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደ ዘለዓለማዊ ነጻነት፤ ከአደፈ፣ ከጎሰቆለ አሮጌ ሕይወት ወደ አዲስ ሕይወት የተሻገርንት ከበዓላት ሁሉ የበለጠ የነጻነት በዓል ነው፡፡
ከዚህም ባሻገር መድኃኒታችን ሞትን በሞቱ ድል ነስቶ፣ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ፣ በሥልጣኑ የተነሣበት ዕለት ነው።

በዓሉ ከሀይማኖታዊ ትውፊት እና ይዘቱ በተጨማሪ ፍጹም የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር ዘወትር ያለመዘንጋት በእምነት በማሰብና እኛም ለሌሎች በተግባር የሚገለጥ ፍቅርን በመስጠት ወንድማማችነትን የምናጠናክርበት፣ ጧሪ እና ደጋፊ የሌላቸው ወገኖቻችን በማሰብና በመደገፍ እንዲሆን እየተመኘን በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታችን እገልጻለሁ፡፡

መልካም የትንሳኤ በዓል!
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ

Join The Discussion

Compare listings

Compare